2 ተሰሎንቄ Chapter 3

For English

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 3 Online

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ተሰሎንቄ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ተሰሎንቄ 3

ምዕራፍ 3

1. በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥

2. እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ።

3. ነገር ግን የሚያጸናችሁ ከክፉውም የሚጠብቃችሁ ጌታ የታመነ ነው።

4. የምናዛችሁንም አሁን እንድታደርጉ ወደ ፊትም ደግሞ እንድታደርጉ ስለ እናንተ በጌታ ታምነናል።

5. ጌታም ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ወደ ክርስቶስም ትዕግሥት ልባችንን ያቅናው።

6. ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።

7. እኛን ልትመስሉ እንዴት እንደሚገባችሁ ራሳችሁ ታውቃላችሁና፤ በእናንተ ዘንድ ያለ ሥርዓት አልሄድንምና፤

8. ከእናንተ ዘንድ በአንዱ ስንኳ እንዳንከብድበት፥ ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ፥ ከማንም እንጀራን እንዲያው አልበላንም።

9. ይህም እኛን ልትመስሉ ራሳችንን እንደ ምሳሌ እንሰጣችሁ ዘንድ ነበር እንጂ፥ ያለ ሥልጣን ስለ ሆንን አይደለም።

10. ደግሞ ከእናንተ ጋር ሳለን። ሊሠራ የማይወድ አይብላ ብለን አዘናችሁ ነበርና።

11. ሥራ ከቶ ሳይሠሩ፥ በሰው ነገር እየገቡ፥ ያለ ሥርዓት ከእናንተ ዘንድ ስለሚሄዱ ስለ አንዳንዶች ሰምተናልና።

12. እንደነዚህ ያሉትንም በጸጥታ እየሠሩ የገዛ እንጀራቸውን ይበሉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እናዛቸዋለን እንመክራቸውማለን።

13. እናንተ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ መልካም ሥራን ለመሥራት አትታክቱ።

14. በዚህ መልእክት ለተላከ ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ተመልከቱት፥ ያፍርም ዘንድ ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።

15. ነገር ግን እንደ ወንድም ገሥጹት እንጂ እንደ ጠላት አትቍጠሩት።

16. የሰላምም ጌታ ራሱ በሁሉ መንገድ ዘወትር ሰላምን ይስጣችሁ። ጌታ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

17. በገዛ እጄ የተጻፈ የእኔ የጳውሎስ ሰላምታ ይህ ነው፤ የመልእክቴ ሁሉ ማስረጃ ይህ ነው፤ እንዲህ እጽፋለሁ።

18. የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችሁ ጋር ይሁን።

About 2 ተሰሎንቄ Chapter 3

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ተሰሎንቄ
Chapter: 3
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ተሰሎንቄ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ተሰሎንቄ Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ተሰሎንቄ Chapter 3?

2 ተሰሎንቄ Chapter 3 is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ተሰሎንቄ Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2 ተሰሎንቄ

  1. 2 ተሰሎንቄ Chapter 2
  2. 2 ተሰሎንቄ Chapter 1

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ዮሐንስ Chapter 5
  2. ቆላስይስ Chapter 1
  3. 1 ተሰሎንቄ Chapter 4
  4. ዮሐንስ Chapter 13
  5. ማርቆስ Chapter 4
  6. ሮሜ Chapter 5
  7. ሉቃስ Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. ኢዩኤል Chapter 2
  2. ፊልጵስዩስ Chapter 4
  3. ማቴዎስ Chapter 17
  4. ዘሌዋውያን Chapter 27
  5. ሕዝቅኤል Chapter 35
  6. ሉቃስ Chapter 7
  7. ሩት Chapter 3
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *