2 ተሰሎንቄ Chapter 2

For English

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 2 Online

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ተሰሎንቄ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ተሰሎንቄ 2

ምዕራፍ 2

1. ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣትና ወደ እርሱ ስለ መሰብሰባችን፥

2. በመንፈስ ወይም በቃል ወይም ከእኛ እንደሚመጣ በመልእክት። የጌታ ቀን ደርሶአል ብላችሁ፥ ከአእምሮአችሁ ቶሎ እንዳትናወጡ እንዳትደነግጡም እንለምናችኋለን።

3. ማንም በማናቸውም መንገድ አያስታችሁ፤ ክህደቱ አስቀድሞ ሳይመጣና የዓመፅ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ ሳይገለጥ፥ አይደርስምና።

4. እኔ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ አዋጅ እየነገረ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እስኪቀመጥ ድረስ፥ አምላክ ከተባለው ሁሉ፥ ሰዎችም ከሚያመልኩት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ የሚያደርገው ተቃዋሚ እርሱ ነው።

5. ገና ከእናንተ ጋር ሳለሁ፥ ይህን እንዳልኋችሁ ትዝ አይላችሁምን?

6. በገዛ ራሱ ጊዜም ይገለጥ ዘንድ፥ የሚከለክለውን አሁን ታውቃላችሁ።

7. የዓመፅ ምሥጢር አሁን ይሠራልና፤ ብቻ ከመንገድ እስኪወገድ ድረስ አሁን የሚከለክል አለ።

8. በዚያም ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በአፉ መንፈስ የሚያጠፋው፥ ሲመጣም በመገለጡ የሚሽረው ዓመፀኛ ይገለጣል፤

9. –

10. ይድኑ ዘንድ የእውነትን ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዓመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።

11. –

12. ስለዚህም ምክንያት፥ በእውነት ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ ይላቸው የነበሩ ሁሉ ፍርድን እንዲቀበሉ፥ ሐሰትን ያምኑ ዘንድ እግዚአብሔር የስሕተትን አሠራር ይልክባቸዋል።

13. እኛ ግን፥ በጌታ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ፥ ሁልጊዜ ስለ እናንተ እግዚአብሔርን ልናመሰግን ግድ አለብን፥ እግዚአብሔር በመንፈስ መቀደስ እውነትንም በማመን ለመዳን እንደ በኵራት መርጦአችኋልና፤

14. ለዚህም የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር ለማግኘት በወንጌላችን ጠራችሁ።

15. እንግዲያስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፥ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ።

16. –

17. ራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና የወደደን በጸጋም የዘላለምን መጽናናት በጎንም ተስፋ የሰጠን እግዚአብሔር አባታችን ልባችሁን ያጽናኑት በበጎም ሥራና በቃል ሁሉ ያጽኑአችሁ።

About 2 ተሰሎንቄ Chapter 2

Read 2 ተሰሎንቄ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ተሰሎንቄ
Chapter: 2
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ተሰሎንቄ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ተሰሎንቄ Chapter 2 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ተሰሎንቄ Chapter 2?

2 ተሰሎንቄ Chapter 2 is part of the Book of 2 ተሰሎንቄ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ተሰሎንቄ Chapter 2 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2 ተሰሎንቄ

  1. 2 ተሰሎንቄ Chapter 1
  2. 2 ተሰሎንቄ Chapter 3

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ጴጥሮስ Chapter 4
  2. ሉቃስ Chapter 21
  3. ሉቃስ Chapter 4
  4. 2 ተሰሎንቄ Chapter 3
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 13
  6. 1 ተሰሎንቄ Chapter 3
  7. 2 ቆሮንቶስ Chapter 11

Related Chapters & Readings

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 13
  2. 1 ጢሞቴዎስ Chapter 2
  3. 1 ዜና መዋዕል Chapter 13
  4. ማርቆስ Chapter 2
  5. ምሳሌ Chapter 24
  6. 1 ነገሥት Chapter 20
  7. 2 ሳሙኤል Chapter 17
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *