1 ጴጥሮስ Chapter 2

For English

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 2 Online

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ጴጥሮስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

1 ጴጥሮስ 2

ምዕራፍ 2

1. እንግዲህ ክፋትን ሁሉ ተንኰልንም ሁሉ ግብዝነትንም ቅንዓትንም ሐሜትንም ሁሉ አስወግዳችሁ፥

2. –

3. ጌታ ቸር መሆኑን ቀምሳችሁ እንደ ሆነ፥ ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።

4. በሰውም ወደ ተጣለ በእግዚአብሔር ዘንድ ግን ወደ ተመረጠና ክቡር ወደ ሆነው ወደ ሕያው ድንጋይ ወደ እርሱ እየቀረባችሁ፥

5. እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።

6. በመጽሐፍ። እነሆ፥ የተመረጠና የከበረን የማዕዘን ራስ ድንጋይ በጽዮን አኖራለሁ በእርሱም የሚያምን አያፍርም ተብሎ ተጽፎአልና።

7. እንግዲህ ክብሩ ለእናንተ ለምታምኑት ነው፤ ለማያምኑ ግን አናጢዎች የጣሉት ድንጋይ እርሱ የማዕዘን ራስ የዕንቅፋትም ድንጋይ የማሰናከያም ዓለት ሆነ፤

8. የማያምኑ ስለ ሆኑ በቃሉ ይሰናከሉበታልና፤ ለዚህ ደግሞ የተመደቡ ናቸው።

9. እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

10. እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

11. ወዳጆች ሆይ፥ ነፍስን ከሚዋጋ ሥጋዊ ምኞት ትርቁ ዘንድ እንግዶችና መጻተኞች እንደ መሆናችሁ እለምናችኋለሁ፤

12. ስለሚመለከቱት ስለ መልካም ሥራችሁ፥ ክፉ እንደምታደርጉ በዚያ እናንተን በሚያሙበት ነገር፥ በሚጎበኝበት ቀን እግዚአብሔርን ያከብሩት ዘንድ በአሕዛብ መካከል ኑሮአችሁ መልካም ይሁን።

13. ስለ ጌታ ብላችሁ ለሰው ሥርዓት ሁሉ ተገዙ፤ ለንጉሥም ቢሆን፥ ከሁሉ በላይ ነውና፤

14. ለመኳንንትም ቢሆን፥ ክፉ የሚያደርጉትን ለመቅጣት በጎም የሚያደርጉትን ለማመስገን ከእርሱ ተልከዋልና ተገዙ።

15. በጎ እያደረጋችሁ፥ የማያውቁትን ሞኞች ዝም ታሰኙ ዘንድ እንዲህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፤

16. አርነት ወጥታችሁ እንደ እግዚአብሔር ባሪያዎች ሁኑ እንጂ ያ አርነት ለክፋት መሸፈኛ እንዲሆን አታድርጉ።

17. ሁሉን አክብሩ፥ ወንድሞችን ውደዱ፥ እግዚአብሔርን ፍሩ፥ ንጉሥን አክብሩ።

18. ሎሌዎች ሆይ፥ ለበጎዎችና ለገሮች ጌቶቻችሁ ብቻ ሳይሆን ለጠማሞች ደግሞ በፍርሃት ሁሉ ተገዙ።

19. በግፍ መከራን የሚቀበል ሰው እግዚአብሔርን እያሰበ ኃዘንን ቢታገሥ ምስጋና ይገባዋልና።

20. ኃጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።

21. የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና፤ ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና።

22. እርሱም ኃጢአት አላደረገም፥ ተንኰልም በአፉ አልተገኘበትም፤

23. ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም መከራንም ሲቀበል አልዛተም፥ ነገር ግን በጽድቅ ለሚፈርደው ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤

24. ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤*ፍ1*

25. በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ። እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበርና፥ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችኋል። ፍ1 በግዕዝ እንዲህ ተጽፎአል። ወበእንተ ኃጣውኢነ ውእቱ ተሰቅለ ዲበ ዕፅ በሥጋሁ ከመ ያውፅአነ እምኃጣውኢነ ወበጽድቁ ያሕይወነ።

About 1 ጴጥሮስ Chapter 2

Read 1 ጴጥሮስ Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 1 ጴጥሮስ
Chapter: 2
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ጴጥሮስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 1 ጴጥሮስ Chapter 2 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 1 ጴጥሮስ Chapter 2?

1 ጴጥሮስ Chapter 2 is part of the Book of 1 ጴጥሮስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 1 ጴጥሮስ Chapter 2 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 1-ጴጥሮስ

  1. 1 ጴጥሮስ Chapter 1
  2. 1 ጴጥሮስ Chapter 3
  3. 1 ጴጥሮስ Chapter 5
  4. 1 ጴጥሮስ Chapter 4

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ኤፌሶን Chapter 4
  2. 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
  3. ማቴዎስ Chapter 25
  4. ያዕቆብ Chapter 5
  5. 1 ዮሐንስ Chapter 4
  6. ያዕቆብ Chapter 3
  7. የሐዋርያት ሥራ Chapter 5

Related Chapters & Readings

  1. ማቴዎስ Chapter 25
  2. ሆሴዕ Chapter 10
  3. 2 ነገሥት Chapter 15
  4. ኢያሱ Chapter 8
  5. ዘሌዋውያን Chapter 20
  6. ዘጸአት Chapter 34
  7. የሐዋርያት ሥራ Chapter 21
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *