ዘዳግም Chapter 25

For English

Read ዘዳግም Chapter 25 Online

Read ዘዳግም Chapter 25 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘዳግም in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘዳግም and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዘዳግም 25

ምዕራፍ 25

1. በሰዎች መካከል ጠብ ቢሆን፥ ወደ ፍርድም ቢመጡ፥ ፈራጆችም ቢፈርዱባቸው፥ ጻድቁን። ደኅና ነህ፥ የበደለውንም። በደለኛ ነህ ይበሉአቸው።

2. ፤ በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቍጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን።

3. ፤ ግርፋቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግርፋት ቢገርፈው ወንድምህ በፊትህ ነውረኛ ይሆናልና ከዚህ በላይ አይጨመርበት።

4. ፤ እህል የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር።

5. ፤ ወንድማማቾች በአንድነት ቢቀመጡ፥ አንዱም ልጅ ሳይኖረው ቢሞት፥ የሞተው ሰው ሚስት ሌላ ሰው ታገባ ዘንድ ወደ ውጭ አትሂድ፤ ነገር ግን የባልዋ ወንድም ወደ እርስዋ ገብቶ እርስዋን ያግባ፥ ከእርስዋም ጋር ይኑር።

6. ፤ የምዋቹ ስም ከእስራኤል ዘንድ እንዳይጠፋ ከእርስዋ የሚወለደው በኵር ልጅ በሞተው በወንድሙ ስም ይጠራ።

7. ፤ ያም ሰው የወንድሙን ሚስት ማግባት ባይወድድ፥ ዋርሳይቱ በበሩ አደባባይ ወደሚቀመጡ ሽማግሌዎች ሄዳ። ዋርሳዬ በእስራኤል ዘንድ ለወንድሙ ስም ማቆም እንቢ አለ፤ ከእኔ ጋር ሊኖርም አልወደደም ትበላቸው።

8. ፤ የከተማውም ሽማግሌዎች ጠርተው ይጠይቁት፤ እርሱም በዚያ ቆሞ። አገባት ዘንድ አልወድድም ቢል፥

9. ፤ ዋርሳይቱ በሽማግሌዎቹ ፊት ወደ እርሱ ቀርባ። የወንድሙን ቤት በማይሠራ ሰው ላይ እንዲህ ይደረግበታል ስትል ጫማውን ከእግሩ ታውጣ፥ በፊቱም እንትፍ ትበልበት።

10. ፤ በእስራኤልም ዘንድ ስሙ የጫማ ፈቱ ቤት ተብሎ ይጠራ።

11. ፤ ሁለት ሰዎች እርስ በርሳቸው ቢጣሉ፥ የአንደኛውም ሚስት ባልዋን ከሚመታው ሰው እጅ ታድነው ዘንድ ብትቀርብ፥ እጅዋንም ዘርግታ ብልቱን ብትይዝ፥

12. ፤ እጅዋን ቍረጥ፥ ዓይንህም አትራራላት።

13. ፤ በከረጢትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት ሚዛን አይኑርልህ።

14. ፤ በቤትህ ውስጥ ታላቅና ታናሽ የሆነ ሁለት ዓይነት መስፈሪያ አይኑርልህ።

15.

16. ፤ ይህን የሚያደርግ ሁሉ ክፋትንም የሚያደርግ ሁሉ በአምላክህ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነውና አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ ይረዝም ዘንድ እውነተኛና ፍጹም ሚዛን ይሁንልህ፤ እውነተኛና ፍጹም መስፈሪያም ይሁንልህ።

17. ፤ ከግብፅ በወጣችሁ ጊዜ አማሌቅ በመንገድ ላይ ያደረገብህን አስብ፤

18. ፤ በመንገድ ላይ እንደ ተቃወመህ፥ አንተም ተስኖህ ደክመህም ሳለህ ከአንተ በኋላ ደክመው የነበሩትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግዚአብሔርንም አልፈራም።

19. ፤ ስለዚህ አምላክህ እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ በሚሰጥህ ምድር ከሚከብቡህ ጠላቶችህ ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ባሳረፈህ ጊዜ፥ የአማሌቅን ዝክረ ስሙን ከሰማይ በታች አጥፋው፤ ይህንን አትርሳ።

About ዘዳግም Chapter 25

Read ዘዳግም Chapter 25 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘዳግም in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዘዳግም
Chapter: 25
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘዳግም. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዘዳግም Chapter 25 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዘዳግም Chapter 25?

ዘዳግም Chapter 25 is part of the Book of ዘዳግም in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዘዳግም Chapter 25 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ዘዳግም

  1. ዘዳግም Chapter 33
  2. ዘዳግም Chapter 3
  3. ዘዳግም Chapter 29
  4. ዘዳግም Chapter 4
  5. ዘዳግም Chapter 30
  6. ዘዳግም Chapter 21
  7. ዘዳግም Chapter 12

Related Chapters & Readings

  1. ሰቆቃወ ኤርምያስ Chapter 1
  2. ኤርምያስ Chapter 26
  3. ኢዮብ Chapter 32
  4. ዮሐንስ Chapter 21
  5. 2 ሳሙኤል Chapter 5
  6. ዘጸአት Chapter 5
  7. 1 ዜና መዋዕል Chapter 8
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *