ገላትያ Chapter 1

For English

Read ገላትያ Chapter 1 Online

Read ገላትያ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ገላትያ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ገላትያ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ገላትያ 1

ምዕራፍ 1

1.

2. በኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታንም ባነሣው በእግዚአብሔር አብ ሐዋርያ የሆነ እንጂ ከሰዎች ወይም በሰው ያልሆነ ጳውሎስ ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤

3. ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታችንም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4. ክፉ ከሆነ ከአሁኑ ዓለም ያድነን ዘንድ እንደ አምላካችንና እንደ አባታችን ፈቃድ ስለ ኃጢአታችን ራሱን ሰጠ።

5. ለአብ ከዘላለም እስከ ዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።

6. በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤

7. እርሱ ግን ሌላ ወንጌል አይደለም፤ የሚያናውጡአችሁ የክርስቶስንም ወንጌል ሊያጣምሙ የሚወዱ አንዳንዶች አሉ እንጂ።

8. ነገር ግን እኛ ብንሆን ወይም ከሰማይ መልአክ፥ ከሰበክንላችሁ ወንጌል የሚለይ ወንጌልን ቢሰብክላችሁ፥ የተረገመ ይሁን።

9. አስቀድመን እንዳልን እንዲሁ አሁን ሁለተኛ እላለሁ፥ ከተቀበላችሁት የተለየውን ማንም ቢሰብክላችሁ የተረገመ ይሁን።

10. ሰውን ወይስ እግዚአብሔርን አሁን እሺ አሰኛለሁን? ወይም ሰውን ደስ ላሰኝ እፈልጋለሁን? አሁን ሰውን ደስ ባሰኝ የክርስቶስ ባሪያ ባልሆንሁም።

11. ወንድሞች ሆይ፥ በእኔ የተሰበከ ወንጌል እንደ ሰው እንዳይደለ አስታውቃችኋለሁ፤

12. ኢየሱስ ክርስቶስ ገልጦልኛል እንጂ እኔ ከሰው አልተቀበልሁትም አልተማርሁትምም።

13. በአይሁድ ሥርዓት በፊት እንዴት እንደ ኖርሁ ሰምታችኋልና፤ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ያለ ልክ አሳድድና አጠፋ ነበር፥

14. ለአባቶችም ወግ ከመጠን ይልቅ እየቀናሁ በወገኔ ዘንድ በዘመኔ ካሉት ብዙዎችን በአይሁድ ሥርዓት እበልጥ ነበር።

15.

16. ነገር ግን በእናቴ ማኅፀን ሳለሁ የለየኝ በጸጋውም የጠራኝ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ፥ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፥

17. ከእኔም በፊት ሐዋርያት ወደ ነበሩት ወደ ኢየሩሳሌም አልወጣሁም፥ ነገር ግን ወደ ዓረብ አገር ሄድሁ እንደ ገናም ወደ ደማስቆ ተመለስሁ።

18. ከዚህ ወዲያ ከሦስት ዓመት በኋላ ኬፋን ልጠይቅ ወደ ኢየሩሳሌም ወጥቼ ከእርሱ ጋር አሥራ አምስት ቀን ሰነበትሁ፤

19. ነገር ግን ከጌታ ወንድም ከያዕቆብ በቀር ከሐዋርያት ሌላ አላየሁም።

20. ስለምፅፍላችሁም ነገር፥ እነሆ፥ በእግዚአብሔር ፊት ሐሰት አልናገርም።

21. ከዚያ ወዲያ ወደ ሶርያና ወደ ኪልቅያ አገር መጣሁ።

22. በክርስቶስም ያሉት የይሁዳ ማኅበሮች ፊቴን አያውቁም ነበር፤

23. ነገር ግን። ቀድሞ እኛን ያሳድድ የነበረ፥ እርሱ በፊት ያጠፋው የነበረውን ሃይማኖት አሁን ይሰብካል ተብሎ ሲነገር ይሰሙ ነበር፤

24. ስለ እኔም እግዚአብሔርን ያከብሩ ነበር።

About ገላትያ Chapter 1

Read ገላትያ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ገላትያ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ገላትያ
Chapter: 1
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ገላትያ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ገላትያ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ገላትያ Chapter 1?

ገላትያ Chapter 1 is part of the Book of ገላትያ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ገላትያ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from አዲስ ኪዳን

  1. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  2. ሉቃስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  7. ሉቃስ Chapter 19

Explore More from ገላትያ

  1. ገላትያ Chapter 2
  2. ገላትያ Chapter 5
  3. ገላትያ Chapter 3
  4. ገላትያ Chapter 6
  5. ገላትያ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. ዘዳግም Chapter 12
  2. 2 ሳሙኤል Chapter 10
  3. ሕዝቅኤል Chapter 43
  4. ምሳሌ Chapter 4
  5. ኤርምያስ Chapter 34
  6. ዘጸአት Chapter 25
  7. 2 ነገሥት Chapter 8
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *