2 ቆሮንቶስ Chapter 5

For English

Read 2 ቆሮንቶስ Chapter 5 Online

Read 2 ቆሮንቶስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ቆሮንቶስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 2 ቆሮንቶስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

2 ቆሮንቶስ 5

ምዕራፍ 5

1. ድንኳን የሚሆነው ምድራዊ መኖሪያችን ቢፈርስ፥ በሰማይ ያለ በእጅ ያልተሠራ የዘላለም ቤት የሚሆን ከእግዚአብሔር የተሠራ ሕንጻ እንዳለን እናውቃለንና።

2. በዚህ ውስጥ በእውነት እንቃትታለንና፥

3. ከሰማይም የሚሆነውን መኖሪያችንን እንድንለብስ እንናፍቃለንና ለብሰን ራቁታችንን አንገኝም።

4. በእውነትም የሚሞተው በሕይወት ይዋጥ ዘንድ ልንለብስ እንጂ ልንገፈፍ የማንወድ ስለ ሆነ፥ በድንኳኑ ያለን እኛ ከብዶን እንቃትታለን።

5. ነገር ግን ለዚሁ የሠራን እግዚአብሔር ነው እርሱም የመንፈሱን መያዣ ሰጠን።

6.

7. እንግዲህ ሁልጊዜ ታምነን፥ በእምነት እንጂ በማየት አንመላለስምና በሥጋ ስናድር ከጌታ ተለይተን በስደት እንዳለን የምናውቅ ከሆንን፥

8. ታምነናል ይልቁንም ከሥጋ ተለይተን በስደት መኖር በጌታም ዘንድ ማደር ደስ ይለናል።

9. ስለዚህ ደግሞ ብናድር ወይም ተለይተን ብንሆን እርሱን ደስ የምናሰኝ ልንሆን እንቀናለን።

10. መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።

11. እንግዲህ የጌታን ፍርሃት አውቀን ሰዎችን እናስረዳለን ለእግዚአብሔር ግን የተገለጥን ነን፤ በሕሊናችሁም ደግሞ የተገለጥን እንደ ሆንን ተስፋ አደርጋለሁ።

12. በመልክ እንጂ በልብ ለማይመኩ የምትመልሱላቸው መልስ እንዲኖራችሁ፥ በእኛ ልትመኩ ምክንያት እንሰጣችኋለን እንጂ ራሳችንን ደግሞ ለእናንተ የምናመሰግን አይደለንም።

13. እብዶች ብንሆን፥ ለእግዚአብሔር ነው፤ ባለ አእምሮዎች ብንሆን፥ ለእናንተ ነው።

14. ይህን ስለቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናልና፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፤

15. በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ።

16. ስለዚህ እኛ ከአሁን ጀምሮ ማንንም በሥጋ እንደሚሆን አናውቅም፤ ክርስቶስንም በሥጋ እንደ ሆነ ያወቅነው ብንሆን እንኳ፥ አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ እንደዚህ አናውቀውም።

17. ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።

18. ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው፤

19. እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ።

20. እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማልድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን።

21. እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።

About 2 ቆሮንቶስ Chapter 5

Read 2 ቆሮንቶስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 2 ቆሮንቶስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: 2 ቆሮንቶስ
Chapter: 5
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 2 ቆሮንቶስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading 2 ቆሮንቶስ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is 2 ቆሮንቶስ Chapter 5?

2 ቆሮንቶስ Chapter 5 is part of the Book of 2 ቆሮንቶስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete 2 ቆሮንቶስ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from 2-ቆሮንቶስ

  1. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  2. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 3
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 10
  7. 2 ቆሮንቶስ Chapter 4

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ዕብራውያን Chapter 13
  2. 2 ጴጥሮስ Chapter 2
  3. ማርቆስ Chapter 9
  4. ዮሐንስ Chapter 19
  5. የሐዋርያት ሥራ Chapter 17
  6. ሮሜ Chapter 16
  7. ሉቃስ Chapter 13

Related Chapters & Readings

  1. ሕዝቅኤል Chapter 21
  2. 1 ነገሥት Chapter 16
  3. ዘጸአት Chapter 39
  4. ዘኍልቍ Chapter 21
  5. ዘፍጥረት Chapter 38
  6. ዘዳግም Chapter 30
  7. መዝሙረ ዳዊት Chapter 73
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *