Read 1 ዮሐንስ Chapter 5 Online
Read 1 ዮሐንስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዮሐንስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ዮሐንስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ዮሐንስ 5
ምዕራፍ 5
1. ክርስቶስ ነው ብሎ በኢየሱስ የሚያምን ሁሉ ከእግዚአብሔር ተወልዶአል፥ ወላጁንም የሚወድ ሁሉ ከእርሱ የተወለደውን ደግሞ ይወዳል።
2. እግዚአብሔርን ስንወድ ትእዛዛቱንም ስናደርግ የእግዚአብሔርን ልጆች እንድንወድ በዚህ እናውቃለን።
3. ትእዛዛቱን ልንጠብቅ የእግዚአብሔር ፍቅር ይህ ነውና፤ ትእዛዛቱም ከባዶች አይደሉም።
4. ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ዓለምን ያሸንፋልና፤ ዓለምንም የሚያሸንፈው እምነታችን ነው።
5. ኢየሱስም የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ከሚያምን በቀር ዓለምን የሚያሸንፍ ማን ነው?
6. በውኃና በደም የመጣ ይህ ነው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ፤ በውኃውና በደሙ እንጂ በውኃው ብቻ አይደለም።
7. መንፈስም እውነት ነውና የሚመሰክረው መንፈስ ነው።
8. የሚመሰክሩት መንፈሱና ውኃው ደሙም ሦስት ናቸውና፤ ሦስቱም በአንድ ይስማማሉ።
9. የሰውን ምስክር ብንቀበል የእግዚአብሔር ምስክር ከእርሱ ይልቅ ይበልጣል፤ ስለ ልጁ የመሰከረው የእግዚአብሔር ምስክር ይህ ነውና።
10. በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።
11. እግዚአብሔርም የዘላለምን ሕይወት እንደ ሰጠን ይህም ሕይወት በልጁ እንዳለ ምስክሩ ይህ ነው።
12. ልጁ ያለው ሕይወት አለው፤ የእግዚአብሔር ልጅ የሌለው ሕይወት የለውም።
13. የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ታውቁ ዘንድ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ለምታምኑ ይህን ጽፌላችኋለሁ።
14. በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል።
15. የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን።
16. ማንም ወንድሙን ሞት የማይገባውን ኃጢአት ሲያደርግ ቢያየው ይለምን፥ ሞትም የማይገባውን ኃጢአት ላደረጉት ሕይወት ይሰጥለታል። ሞት የሚገባው ኃጢአት አለ፤ ስለዚያ እንዲጠይቅ አልልም።
17. ዓመፃ ሁሉ ኃጢአት ነው፥ ሞትም የማይገባው ኃጢአት አለ።
18. ከእግዚአብሔር የተወለደ ሁሉ ኃጢአትን እንዳያደርግ፥ ነገር ግን ከእግዚአብሔር የተወለደው ራሱን እንዲጠብቅ ክፉውም እንዳይነካው እናውቃለን።
19. ከእግዚአብሔር እንደ ሆንን ዓለምም በሞላው በክፉው እንደ ተያዘ እናውቃለን።
20. የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።
21. ልጆች ሆይ፥ ከጣዖታት ራሳችሁን ጠብቁ።
About 1 ዮሐንስ Chapter 5
Read 1 ዮሐንስ Chapter 5 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ዮሐንስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ዮሐንስ
Chapter: 5
Testament: New Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ዮሐንስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ዮሐንስ Chapter 5 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ዮሐንስ Chapter 5?
1 ዮሐንስ Chapter 5 is part of the Book of 1 ዮሐንስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ዮሐንስ Chapter 5 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1-ዮሐንስ
Explore More from አዲስ ኪዳን
- ሉቃስ Chapter 13
- ሮሜ Chapter 13
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 1
- 2 ቆሮንቶስ Chapter 8
- ማቴዎስ Chapter 28
- የሐዋርያት ሥራ Chapter 13
- ፊልጵስዩስ Chapter 4