ኤፌሶን Chapter 2

For English

Read ኤፌሶን Chapter 2 Online

Read ኤፌሶን Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤፌሶን in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ኤፌሶን and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ኤፌሶን 2

ምዕራፍ 2

1. በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእነርሱም፥

2. በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፥ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሠራው መንፈስ አለቃ እንደ ሆነው በአየር ላይ ሥልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፥ በፊት ተመላለሳችሁባቸው።

3. በእነዚህም ልጆች መካከል እኛ ሁላችን ደግሞ፥ የሥጋችንንና የልቡናችንን ፈቃድ እያደረግን፥ በሥጋችን ምኞት በፊት እንኖር ነበርን እንደ ሌሎቹም ደግሞ ከፍጥረታችን የቁጣ ልጆች ነበርን።

4. ነገር ግን እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለ ጠጋ ስለ ሆነ፥

5. ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን፥ በጸጋ ድናችኋልና፥

6. –

7. በሚመጡ ዘመናትም በክርስቶስ ኢየሱስ ለእኛ ባለው ቸርነት ከሁሉ የሚበልጠውን የጸጋውን ባለ ጠግነት ያሳይ ዘንድ፥ ከእርሱ ጋር አስነሣን በክርስቶስ ኢየሱስም በሰማያዊ ስፍራ ከእርሱ ጋር አስቀመጠን።

8. ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤

9. ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም።

10. እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን።

11. ስለዚህ እናንተ አስቀድሞ በሥጋ አሕዛብ የነበራችሁ፥ በሥጋ በእጅ የተገረዙ በተባሉት ያልተገረዙ የተባላችሁ፥ ይህን አስቡ፤

12. በዚያ ዘመን ከእስራኤል መንግሥት ርቃችሁ ለተስፋውም ቃል ኪዳን እንግዶች ሆናችሁ በዚህም ዓለም ተስፋን አጥታችሁ ከእግዚአብሔርም ተለይታችሁ ያለ ክርስቶስ ነበራችሁ።

13. አሁን ግን እናንተ በፊት ርቃችሁ የነበራችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆናችሁ በክርስቶስ ደም ቀርባችኋል።

14. –

15. እርሱ ሰላማችን ነውና፤ ሁለቱን ያዋሐደ በአዋጅ የተነገሩትንም የትእዛዛትን ሕግ ሽሮ በመካከል ያለውን የጥል ግድግዳን በሥጋው ያፈረሰ፤ ይህም ከሁለታቸው አንድን አዲስን ሰው በራሱ ይፈጥር ዘንድ ሰላምንም ያደርግ ዘንድ፥

16. ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ በእርሱ ሁለታቸውን በአንድ አካል ከእግዚአብሔር ጋር ያስታርቅ ዘንድ ነው።

17. መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤

18. በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።

19. እንግዲያስ ከእንግዲህ ወዲህ ከቅዱሳን ጋር ባላገሮችና የእግዚአብሔር ቤተ ሰዎች ናችሁ እንጂ እንግዶችና መጻተኞች አይደላችሁም።

20. በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፥ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤

21. በእርሱም ሕንጻ ሁሉ እየተጋጠመ በጌታ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን ያድጋል፤

22. በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።

About ኤፌሶን Chapter 2

Read ኤፌሶን Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ኤፌሶን in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ኤፌሶን
Chapter: 2
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ኤፌሶን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ኤፌሶን Chapter 2 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ኤፌሶን Chapter 2?

ኤፌሶን Chapter 2 is part of the Book of ኤፌሶን in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ኤፌሶን Chapter 2 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from አዲስ ኪዳን

  1. ሉቃስ Chapter 7
  2. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  7. ሉቃስ Chapter 19

Explore More from ኤፌሶን

  1. ኤፌሶን Chapter 5
  2. ኤፌሶን Chapter 6
  3. ኤፌሶን Chapter 1
  4. ኤፌሶን Chapter 4
  5. ኤፌሶን Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. ሮሜ Chapter 15
  2. 2 ነገሥት Chapter 20
  3. ዘጸአት Chapter 17
  4. ኢሳይያስ Chapter 34
  5. አስቴር Chapter 4
  6. ዘኍልቍ Chapter 3
  7. ማቴዎስ Chapter 6
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *