Read ዘሌዋውያን Chapter 2 Online
Read ዘሌዋውያን Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዘሌዋውያን and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
ዘሌዋውያን 2
ምዕራፍ 2
1. ማናቸውም ሰው የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ሲያቀርብ ቍርባኑ ከመልካም ዱቄት ይሁን፤ ዘይትም ያፈስስበታል፥ ዕጣንም ይጨምርበታል፤
2. ፤ ወደ አሮንም ልጆች ወደ ካህናቱ ያመጣዋል፤ ከመልካም ዱቄቱና ከዘይቱም አንድ እፍኝ ሙሉና ዕጣኑን ሁሉ ወስዶ ካህኑ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን ለመታሰቢያ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
3. ፤ ከእህሉም ቍርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚሆን የእሳት ቍርባን ቅዱስ ቅዱሳን ነው።
4. ፤ በእቶን የተጋገረውን የእህል ቍርባን ስታቀርብ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት የቂጣ እንጐቻ ወይም በዘይት የተቀባ ስስ ቂጣ ይሁን።
5. ፤ ቍርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን።
6. ፤ ቈርሰህም ዘይት ታፈስስበታለህ፤ የእህል ቍርባን ነው።
7. ፤ ቍርባንህም በመቀቀያ የበሰለ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ ዘይት የገባበት ከመልካም ዱቄት የተደረገ ይሁን።
8. ፤ ከዚህም የተደረገውን የእህል ቍርባን ወደ እግዚአብሔር ታመጣለህ፤ ለካህኑም ይሰጣል፥ እርሱም ወደ መሠዊያው ያቀርበዋል።
9. ፤ ካህኑም ከእህሉ ቍርባን መታሰቢያውን አንሥቶ የእሳት ቍርባን ለእግዚአብሔር ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።
10. ፤ ከእህሉም ቍርባን የተረፈው ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል፤ ይህም ለእግዚአብሔር የሚሆን የእሳት ቍርባን ቅዱስ ቅዱሳን ነው።
11. ፤ እርሾ ያለበት ነገር ማርም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ይሆን ዘንድ አታቀርቡምና ለእግዚአብሔር የምታቀርቡት የእህል ቍርባን ሁሉ እርሾ አይሁንበት።
12. ፤ እነዚህንም የበኵራት ቍርባን አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፤ እንደ ጣፋጭ ሽታ ግን በመሠዊያው ላይ አይቃጠሉም።
13. ፤ የምታቀርበውን የእህል ቍርባን ሁሉ በጨው ታጣፍጠዋለህ፤ የአምላክህንም ቃል ኪዳን ጨው ከእህል ቍርባንህ አታጐድልም፤ በቍርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ታቀርባለህ።
14. ፤ ከበኵራትም የእህል ቍርባን ለእግዚአብሔር ብታቀርብ ስለዚህ ቍርባን በእሳት የተጠበሰና የተፈተገ የእህል እሸት ታቀርባለህ።
15. ፤ ዘይትም ታፈስስበታለህ፥ ዕጣንም ትጨምርበታለህ፤ የእህል ቍርባን ነው።
16. ፤ ካህኑም ከተፈተገው እህል ከዘይቱም ወስዶ ከዕጣኑ ሁሉ ጋር መታሰቢያውን ያቃጥላል፤ ይህ ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነው።
About ዘሌዋውያን Chapter 2
Read ዘሌዋውያን Chapter 2 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: ዘሌዋውያን
Chapter: 2
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዘሌዋውያን. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading ዘሌዋውያን Chapter 2 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is ዘሌዋውያን Chapter 2?
ዘሌዋውያን Chapter 2 is part of the Book of ዘሌዋውያን in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete ዘሌዋውያን Chapter 2 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from ብሉይ ኪዳን
Explore More from ዘሌዋውያን
- ዘሌዋውያን Chapter 1
- ዘሌዋውያን Chapter 14
- ዘሌዋውያን Chapter 22
- ዘሌዋውያን Chapter 25
- ዘሌዋውያን Chapter 5
- ዘሌዋውያን Chapter 6
- ዘሌዋውያን Chapter 12