ዮሐንስ Chapter 15

For English

Read ዮሐንስ Chapter 15 Online

Read ዮሐንስ Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዮሐንስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዮሐንስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዮሐንስ 15

ምዕራፍ 15

1. እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ ገበሬውም አባቴ ነው።

2. ፍሬ የማያፈራውን በእኔ ያለውን ቅርንጫፍ ሁሉ ያስወግደዋል፤ ፍሬ የሚያፈራውንም ሁሉ አብዝቶ እንዲያፈራ ያጠራዋል።

3. እናንተ ስለ ነገርኋችሁ ቃል አሁን ንጹሐን ናችሁ፤

4. በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም።

5. እኔ የወይን ግንድ ነኝ እናንተም ቅርንጫፎች ናችሁ። ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ አትችሉምና በእኔ የሚኖር እኔም በእርሱ፥ እርሱ ብዙ ፍሬ ያፈራል።

6. በእኔ የማይኖር ቢሆን እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል ይደርቅማል፤ እነርሱንም ሰብስበው ወደ እሳት ይጥሉአቸዋል፥ ያቃጥሉአቸውማል።

7. በእኔ ብትኖሩ ቃሎቼም በእናንተ ቢኖሩ የምትወዱትን ሁሉ ለምኑ ይሆንላችሁማል።

8. ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከበራል።

9. አብ እንደ ወደደኝ እኔ ደግሞ ወደድኋችሁ፤ በፍቅሬ ኑሩ።

10. እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ በፍቅሩም እንደምኖር፥ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ።

11. ደስታዬም በእናንተ እንዲሆን ደስታችሁም እንዲፈጸም ይህን ነግሬአችኋለሁ።

12. እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት።

13. ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።

14. እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ።

15. ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።

16. እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንዲሰጣችሁ፥ ልትሄዱና ፍሬ ልታፈሩ ፍሬአችሁም ሊኖር ሾምኋችሁ።

17. እርስ በርሳችሁ እንድትዋደዱ ይህን አዛችኋለሁ።

18. ዓለም ቢጠላችሁ ከእናንተ በፊት እኔን እንደ ጠላኝ እወቁ።

19. ከዓለምስ ብትሆኑ ዓለም የራሱ የሆነውን ይወድ ነበር፤ ነገር ግን እኔ ከዓለም መረጥኋችሁ እንጂ ከዓለም ስለ አይደላችሁ ስለዚህ ዓለም ይጠላችኋል።

20. ባርያ ከጌታው አይበልጥም ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን አሳደውኝ እንደ ሆኑ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌን ጠብቀው እንደ ሆኑ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።

21. ዳሩ ግን የላከኝን አያውቁምና ይህን ሁሉ ሰለ ስሜ ያደርጉባችኋል።

22. እኔ መጥቼ ባልነገርኋቸውስ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም።

23. እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል።

24. ሌላ ሰው ያላደረገውን ሥራ በመካከላቸው ባላደረግሁ፥ ኃጢአት ባልሆነባቸውም ነበር፤ አሁን ግን እኔንም አባቴንም አይተውማል ጠልተውማል።

25. ነገር ግን በሕጋቸው። በከንቱ ጠሉኝ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነው።

26. ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤

27. እናንተም ደግሞ ከመጀመሪያ ከእኔ ጋር ኖራችኋልና ትመሰክራላችሁ።

About ዮሐንስ Chapter 15

Read ዮሐንስ Chapter 15 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዮሐንስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዮሐንስ
Chapter: 15
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዮሐንስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዮሐንስ Chapter 15 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዮሐንስ Chapter 15?

ዮሐንስ Chapter 15 is part of the Book of ዮሐንስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዮሐንስ Chapter 15 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from አዲስ ኪዳን

  1. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  2. ሉቃስ Chapter 7
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 7
  4. 2 ቆሮንቶስ Chapter 5
  5. 2 ቆሮንቶስ Chapter 2
  6. 2 ቆሮንቶስ Chapter 6
  7. 2 ቆሮንቶስ Chapter 3

Explore More from ዮሐንስ

  1. ዮሐንስ Chapter 14
  2. ዮሐንስ Chapter 3
  3. ዮሐንስ Chapter 1
  4. ዮሐንስ Chapter 10
  5. ዮሐንስ Chapter 21
  6. ዮሐንስ Chapter 12
  7. ዮሐንስ Chapter 4

Related Chapters & Readings

  1. መዝሙረ ዳዊት Chapter 133
  2. ዘፍጥረት Chapter 23
  3. ኢዮብ Chapter 36
  4. ምሳሌ Chapter 9
  5. 1 ሳሙኤል Chapter 4
  6. ማቴዎስ Chapter 28
  7. ምሳሌ Chapter 30
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *