ዕንባቆም Chapter 3

For English

Read ዕንባቆም Chapter 3 Online

Read ዕንባቆም Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዕንባቆም in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ዕንባቆም and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ዕንባቆም 3

ምዕራፍ 3

1. የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር።

2. ፤ አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፤ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፤ በዓመታት መካከል ትታወቅ፤ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።

3. ፤ እግዚአብሔር ከቴማን፥ ቅዱሱም ከፋራን ተራራ ይመጣል። ክብሩ ሰማያትን ከድኖአል፥ ምስጋናውም ምድርን ሞልቶአል።

4. ፤ ፀዳሉም እንደ ብርሃን ነው፤ ጨረር ከእጁ ወጥቶአል፤ ኃይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

5. ፤ ቸነፈር በፊቱ ይሄዳል፥ የእሳትም ነበልባል ከእግሩ ይወጣል።

6. ፤ ቆመ፥ ምድርንም አወካት፤ ተመለከተ፥ አሕዛብንም አናወጠ፤ የዘላለምም ተራሮች ተቀጠቀጡ፥ የዘላለምም ኮረብቶች ቀለጡ፤ መንገዱ ከዘላለም ነው።

7. ፤ የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ አየሁ፤ የምድያም አገር መጋረጃዎች ተንቀጠቀጡ።

8. ፤ በውኑ እግዚአብሔር በወንዞች ላይ ተቈጥቶአልን? ቍጣህ በወንዞች ላይ፥ መዓትህም በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህና በማዳንህ ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።

9. ፤ በቃልህ እንደ ማልህ መቅሠፍትህን አወጣህ፤ ቀስትህንም ገተርህ፤ ምድርን ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ።

10. ፤ ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ፤ የውኃ ሞገድ አልፎአል፤ ቀላዩም ድምፁን ሰጥቶአል፥ እጁንም ወደ ላይ አንሥቶአል።

11. ፤ ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሃን የተነሣ፥ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ፀዳል የተነሣ፥ ፀሐይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ።

12. ፤ በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፤ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው።

13. ፤ ሕዝብህን ለመታደግ፥ የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤ የኃጢአተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ፤ መሠረቱን እስከ አንገቱ ድረስ ገለጥህ።

14. ፤ የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ፤ እኔን ይበትኑ ዘንድ እንደ ዐውሎ ነፋስ መጡ፤ ችግረኛውን በስውር ለመዋጥ ደስታቸው ነው።

15. ፤ ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ።

16. ፤ እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፤ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፤ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፤ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።

17. ፤ ምንም እንኳ በለስም ባታፈራ፥ በወይንም ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፥ የወይራ ሥራ ቢጐድል፥ እርሾችም መብልን ባይሰጡ፥ በጎች ከበረቱ ቢጠፉ፥ ላሞችም በጋጡ ውስጥ ባይገኙ፥

18. ፤ እኔ ግን በእግዚአብሔር ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።

19. ፤ ጌታ እግዚአብሔር ኃይሌ ነው፤ እግሮቼን እንደ ዋላ እግሮች ያደርጋል፤ በከፍታዎችም ላይ ያስሄደኛል።

About ዕንባቆም Chapter 3

Read ዕንባቆም Chapter 3 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ዕንባቆም in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ዕንባቆም
Chapter: 3
Testament: Old Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ዕንባቆም. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ዕንባቆም Chapter 3 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ዕንባቆም Chapter 3?

ዕንባቆም Chapter 3 is part of the Book of ዕንባቆም in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ዕንባቆም Chapter 3 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ብሉይ ኪዳን

  1. አሞጽ Chapter 4
  2. አሞጽ Chapter 1
  3. አሞጽ Chapter 3
  4. አሞጽ Chapter 6
  5. አሞጽ Chapter 2
  6. አሞጽ Chapter 7
  7. አሞጽ Chapter 5

Explore More from ዕንባቆም

  1. ዕንባቆም Chapter 1
  2. ዕንባቆም Chapter 2

Related Chapters & Readings

  1. ኤርምያስ Chapter 27
  2. ማቴዎስ Chapter 21
  3. መሳፍንት Chapter 21
  4. ዕብራውያን Chapter 6
  5. ዕዝራ Chapter 4
  6. ራእይ Chapter 15
  7. 1 ጴጥሮስ Chapter 2
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *