ሉቃስ Chapter 19

For English

Read ሉቃስ Chapter 19 Online

Read ሉቃስ Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሉቃስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ሉቃስ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

A+ A A-

ሉቃስ 19

ምዕራፍ 19

1. ወደ ኢያሪኮም ገብቶ ያልፍ ነበር። እነሆም ዘኬዎስ የሚባል ሰው፥

2. እርሱም የቀራጮች አለቃ ነበረ፥ ባለ ጠጋም ነበረ።

3. ኢየሱስንም የትኛው እንደ ሆነ ሊያይ ይፈልግ ነበር፤ ቁመቱም አጭር ነበረና ስለ ሕዝቡ ብዛት አቃተው።

4. በዚያችም መንገድ ያልፍ ዘንድ አለውና ያየው ዘንድ ወደ ፊት ሮጦ በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።

5. ኢየሱስም ወደዚያ ስፍራ በደረሰ ጊዜ፥ አሻቅቦ አየና። ዘኬዎስ ሆይ፥ ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛልና ፈጥነህ ውረድ አለው።

6. ፈጥኖም ወረደ በደስታም ተቀበለው።

7. ሁሉም አይተው። ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ሊውል ገባ ብለው አንጐራጐሩ።

8. ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን። ጌታ ሆይ፥ ካለኝ ሁሉ እኵሌታውን ለድሆች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደ ሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ አለው።

9. ኢየሱስም። እርሱ ደግሞ የአብርሃም ልጅ ነውና ዛሬ ለዚህ ቤት መዳን ሆኖለታል፤

10. የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቶአለና አለው።

11. እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።

12. ስለዚህም እንዲህ አላቸው። አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።

13. አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና። እስክመጣ ድረስ ነግዱ አላቸው።

14. የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና። ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ።

15. መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ።

16. የፊተኛውም ደርሶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ አለው።

17. እርሱም። መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው።

18. ሁለተኛውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ አለው።

19. ይህንም ደግሞ። አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው።

20. ሌላውም መጥቶ። ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤

21. ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ አለው።

22. እርሱም። አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው?

23. እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር አለው።

24. በዚያም ቆመው የነበሩትን። ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት አላቸው።

25. እነርሱም። ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው አሉት።

26. እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል።

27. ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው።

28. ይህንም ከተናገረ በኋላ፥ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ይቀድማቸው ነበር።

29. ደብረ ዘይትም በሚባል ተራራ አጠገብ ወዳሉት ወደ ቤተ ፋጌና ወደ ቢታንያ በቀረበ ጊዜ፥ ከደቀ መዛሙርቱ ሁለቱን ላከና።

30. በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ፥ ወደ እርስዋም ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበት ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ፥ ፈትታችሁም አምጡት።

31. ማንም። ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? ብሎ ቢጠይቃችሁ፥ እንዲሁ። ለጌታ ያስፈልገዋል በሉ አላቸው።

32. የተላኩትም ሄደው እንዳላቸው አገኙ።

33. እነርሱም ውርንጫውን ሲፈቱ ጌቶቹ። ውርንጫውን ስለ ምን ትፈቱታላችሁ? አሉአቸውም

34. እነርሱም። ለጌታ ያስፈልገዋል አሉ።

35. ወደ ኢየሱስም አመጡት፥ በውርንጫውም ላይ ልብሳቸውን ጭነው ኢየሱስን አስቀመጡት።

36. ሲሄድም ልብሳቸውን በመንገድ ያነጥፉ ነበር።

37. ወደ ደብረ ዘይት ቍልቍለትም አሁን በቀረበ ጊዜ፥ ደቀ መዛሙርቱ ሁላቸው ደስ እያላቸው ተአምራትን ሁሉ ስላዩ በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን ሊያመሰግኑ ጀምረው።

38. በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያምም ክብር አሉ።

39. ከሕዝብም መካከል ከፈሪሳውያን አንዳንዱ። መምህር ሆይ፥ ደቀ መዛሙርትህን ገሥጻቸው አሉት።

40. መልሶም። እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።

41. ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ አለቀሰላት፥

42. እንዲህ እያለ። ለሰላምሽ የሚሆነውን በዚህ ቀን አንቺስ ስንኳ ብታውቂ፤ አሁን ግን ከዓይንሽ ተሰውሮአል።

43. ወራት ይመጣብሻልና፥ ጠላቶችሽም ቅጥር ይቀጥሩብሻል ይከቡሻልም በየበኵሉም ያስጨንቁሻል፤

44. አንቺንም በአንቺም ውስጥ የሚኖሩትን ልጆችሽን ወደ ታች ይጥላሉ፥ በአንቺ ውስጥም ድንጋይ በድንጋይ ላይ አይተዉም፥ የመጐብኘትሽን ዘመን አላወቅሽምና።

45. ወደ መቅደስም ገብቶ በእርሱ የሚሸጡትን የሚገዙትንም ያወጣ ጀመር፤

46. እርሱም። ቤቴ የጸሎት ቤት ይሆናል ተብሎ ተጽፎአል፤ እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችሁት አላቸው።

47. ዕለት ዕለትም በመቅደስ ያስተምር ነበር፤ ነገር ግን የካህናት አለቆችና ጻፎች የሕዝቡ ታላላቆችም ሊገድሉት ይፈልጉ ነበር፥

48. የሚያደርጉበትንም አጡ፤ ሕዝቡ ሁሉ ሲሰሙት ተንጠልጥለውበት ነበርና።

About ሉቃስ Chapter 19

Read ሉቃስ Chapter 19 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ሉቃስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ሉቃስ
Chapter: 19
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ሉቃስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ሉቃስ Chapter 19 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ሉቃስ Chapter 19?

ሉቃስ Chapter 19 is part of the Book of ሉቃስ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ሉቃስ Chapter 19 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ሉቃስ

  1. ሉቃስ Chapter 7
  2. ሉቃስ Chapter 20
  3. ሉቃስ Chapter 11
  4. ሉቃስ Chapter 2
  5. ሉቃስ Chapter 21
  6. ሉቃስ Chapter 12
  7. ሉቃስ Chapter 1

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. 1 ቆሮንቶስ Chapter 3
  2. ሉቃስ Chapter 11
  3. 2 ቆሮንቶስ Chapter 1
  4. የሐዋርያት ሥራ Chapter 9
  5. 1 ቆሮንቶስ Chapter 7
  6. 1 ጴጥሮስ Chapter 4
  7. ራእይ Chapter 3

Related Chapters & Readings

  1. ናሆም Chapter 2
  2. ነህምያ Chapter 10
  3. 2 ጴጥሮስ Chapter 1
  4. መዝሙረ ዳዊት Chapter 90
  5. ማርቆስ Chapter 7
  6. ቆላስይስ Chapter 4
  7. ሆሴዕ Chapter 1
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *