Read 3 ዮሐንስ Chapter 1 Online
Read 3 ዮሐንስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 3 ዮሐንስ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 3 ዮሐንስ and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
3 ዮሐንስ 1
ምዕራፍ 1
1. ሽማግሌው በእውነት እኔ ለምወደው ለተወደደው ለጋይዮስ።
2. ወዳጅ ሆይ፥ ነፍስህ እንደሚከናወን፥ በነገር ሁሉ እንዲከናወንልህና ጤና እንዲኖርህ እጸልያለሁ።
3. ወንድሞች መጥተው አንተ በእውነት እንደምትሄድ ስለ እውነትህ ሲመሰክሩ እጅግ ደስ ብሎኛልና።
4. ልጆቼ በእውነት እንዲሄዱ ከመስማት ይልቅ የሚበልጥ ደስታ የለኝም።
5. ወዳጅ ሆይ፥ ምንም እንግዶች ቢሆኑ፥ ለወንድሞች በምታደርገው ሁሉ የታመነ ሥራ ትሠራለህ፥ እነርሱም በማኅበር ፊት ስለ ፍቅርህ መስክረዋል፤
6. ለእግዚአብሔር እንደሚገባ አድርገህ በጉዞአቸው ብትረዳ መልካም ታደርጋለህ፤
7. ከአሕዛብ አንዳች ሳይቀበሉ ስለ ስሙ ወጥተዋልና።
8. እንግዲህ ከእውነት ጋር አብረን እንድንሠራ እኛ እንዲህ ያሉትን በእንግድነት ልንቀበል ይገባናል።
9. ወደ ቤተ ክርስቲያን ጻፍሁ፤ ዳሩ ግን ዋናቸው ሊሆን የሚወድ ዲዮጥራጢስ አይቀበለንም።
10. ስለዚህ፥ እኔ ብመጣ፥ በእኛ ላይ በክፉ ቃል እየለፈለፈ የሚያደርገውን ሥራውን አሳስባለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፥ ሊቀበሉአቸውም የሚወዱትን ከልክሎ ከቤተ ክርስቲያን ያወጣቸዋል።
11. ወዳጅ ሆይ፥ በጎ የሆነውን እንጂ ክፉን አትምሰል። በጎ የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው፤ ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።
12. ለድሜጥሮስ ሁሉ ይመሰክሩለታል፥ እውነት ራስዋም ትመሰክርለታለች፤ እኛም ደግሞ እንመሰክርለታለን፥ ምስክርነታችንም እውነት እንደ ሆነ ታውቃላችሁ።
13. ልጽፍልህ የምፈልገው ብዙ ነገር ነበረኝ፥ ዳሩ ግን በቀለምና በብርዕ ልጽፍልህ አልወድም፤
14. ነገር ግን ወዲያው ላይህ ተስፋ አደርጋለሁ፥ አፍ ለአፍም እንነጋገራለን። [15] ሰላም ለአንተ ይሁን። ወዳጆች ሰላምታ ያቀርቡልሃል። ወዳጆችን በየስማቸው እየጠራህ ሰላምታ አቅርብልኝ።
About 3 ዮሐንስ Chapter 1
Read 3 ዮሐንስ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 3 ዮሐንስ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 3 ዮሐንስ
Chapter: 1
Testament: New Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 3 ዮሐንስ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 3 ዮሐንስ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 3 ዮሐንስ Chapter 1?
3 ዮሐንስ Chapter 1 is part of the Book of 3 ዮሐንስ in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 3 ዮሐንስ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 3 ዮሐንስ
Explore More from አዲስ ኪዳን
- 2 ጢሞቴዎስ Chapter 4
- ፊልጵስዩስ Chapter 4
- 2 ቆሮንቶስ Chapter 13
- 1 ቆሮንቶስ Chapter 13
- ሉቃስ Chapter 19
- ቆላስይስ Chapter 4
- ማቴዎስ Chapter 20