Read 1 ሳሙኤል Chapter 11 Online
Read 1 ሳሙኤል Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of 1 ሳሙኤል and the Holy Bible online.
Choose a Chapter
1 ሳሙኤል 11
ምዕራፍ 11
1. እንዲህም ሆነ፤ ከአንድ ወር በኋላ አሞናዊው ናዖስ ወጣ፥ በኢያቢስ ገለዓድም ሰፈረ፤ የኢያቢስም ሰዎች ሁሉ። ቃል ኪዳን አድርግልን፥ እኛም እንገዛልሃለን አሉት።
2. ፤ አሞናዊውም ናዖስ። ቀኝ ዓይናችሁን ሁሉ በማውጣት ቃል ኪዳን አደርግላችኋለሁ፤ በእስራኤልም ሁሉ ላይ ስድብ አደረጋለሁ አላቸው።
3. ፤ የኢያቢስም ሽማግሌዎች። ወደ እስራኤል አገር ሁሉ መልክተኞችን እንድንልክ ሰባት ቀን ቆይልን፤ ከዚያም በኋላ የሚያድነን ባይኖር ወደ አንተ እንመጣለን አሉት።
4. ፤ መልክተኞቹም ሳኦል ወዳለበት ወደ ጊብዓ መጥተው ይህን ነገር በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ፤ ሕዝቡም ሁሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ።
5. ፤ እነሆም፥ ሳኦል በሬዎቹን ተከትሎ ከእርሻው መጣ፤ ሳኦልም። ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው? አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት።
6. ፤ ይህንም ነገር በሰማው ጊዜ በሳኦል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ በኃይል ወረደ፥ ቍጣውም እጅግ ነደደ።
7. ፤ ጥምዱንም በሬዎች ወስዶ ቈራረጣቸው፥ ወደ እስራኤልም ዳርቻ ሁሉ በመልክተኞቹ እጅ ሰደደና። ሳኦልንና ሳሙኤልን ተከትሎ የማይወጣ ሁሉ፥ በበሬዎቹ እንዲሁ ይደረግ አለ። ድንጋጤም በሕዝቡ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ወደቀ፥ እንደ አንድ ሰውም ሆነው ወጡ።
8. ፤ በቤዜቅም ቈጠራቸው፤ የእስራኤልም ልጆች ሦስት መቶ ሺህ፥ የይሁዳም ሰዎች ሠላሳ ሺህ ነበሩ።
9. ፤ የመጡትንም መልክተኞች። የኢያቢስ ገለዓድን ሰዎች። ነገ ፀሐይ በተኮሰ ጊዜ ማዳን ይሆንላችኋል በሉአቸው አሉአቸው። መልክተኞችም መጥተው ለኢያቢስ ሰዎች ነገሩ፤ ደስም አላቸው።
10. ፤ የአያቢስም ሰዎች። ነገ እንወጣላችኋለን፥ ደስ የሚያሰኛችሁንም አድርጉብን አሉ።
11. ፤ በነጋውም ሳኦል ሕዝቡን በሦስት ወገን አደረጋቸው፤ ወገግም ባለ ጊዜ ወደ ሰፈሩ መካከል ገቡ፥ ቀትርም እስኪሆን ድረስ አሞናውያንን መቱ፤ የቀሩትም ተበተኑ፥ ሁለትም በአንድ ላይ ሆነው አልቀሩላቸውም።
12. ፤ ሕዝቡም ሳሙኤልን። ሳኦል አይንገሥብን ያሉ እነማናቸው? አውጡአቸውና እንግደላቸው አሉት።
13. ፤ ሳኦልም። ዛሬ እግዚአብሔር ለእስራኤል ማዳን አድርጎአልና ዛሬ አንድ ሰው አይሞትም አለ።
14. ፤ ሳሙኤልም ሕዝቡን። ኑ፥ ወደ ጌልገላ እንሂድ፥ በዚያም መንግሥቱን እናድስ አላቸው።
15. ፤ ሕዝቡም ሁሉ ወደ ጌልገላ ሄዱ፥ በዚያም ሳኦልን በእግዚአብሔር ፊት በጌልገላ አነገሡት፤ በዚያም በእግዚአብሔር ፊት የደኅንነት መሥዋዕት አቀረቡ፤ በዚያም ሳኦልና የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታ አደረጉ።
About 1 ሳሙኤል Chapter 11
Read 1 ሳሙኤል Chapter 11 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Old Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.
Book Information
Book: 1 ሳሙኤል
Chapter: 11
Testament: Old Testament
How to Read this Chapter
Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading 1 ሳሙኤል. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.
More Resources
Continue Reading the Bible
Continue reading 1 ሳሙኤል Chapter 11 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.
Frequently Asked Questions
What is 1 ሳሙኤል Chapter 11?
1 ሳሙኤል Chapter 11 is part of the Book of 1 ሳሙኤል in the Holy Bible.
Can I read this chapter online?
Yes. You can read the complete 1 ሳሙኤል Chapter 11 online for free with easy chapter navigation.
More Chapters from 1 ሳሙኤል
- 1 ሳሙኤል Chapter 22
- 1 ሳሙኤል Chapter 20
- 1 ሳሙኤል Chapter 9
- 1 ሳሙኤል Chapter 3
- 1 ሳሙኤል Chapter 13
- 1 ሳሙኤል Chapter 30
- 1 ሳሙኤል Chapter 23
Explore More from ብሉይ ኪዳን
- 2 ዜና መዋዕል Chapter 34
- ኢዮብ Chapter 19
- ዘኍልቍ Chapter 5
- መዝሙረ ዳዊት Chapter 97
- ዘኍልቍ Chapter 21
- ዘዳግም Chapter 26
- ዘኍልቍ Chapter 33