ቲቶ Chapter 1

For English

Read ቲቶ Chapter 1 Online

Read ቲቶ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ቲቶ in the New Testament. Browse every verse with easy chapter navigation, continue to the next chapter, or explore the complete Book of ቲቶ and the Holy Bible online.

Choose a Chapter

ቲቶ 1

ምዕራፍ 1

1. የእግዚአብሔር ባሪያና የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥

2. በእግዚአብሔር ለተመረጡት እምነት እንዲሆንላቸው በዘላለምም ሕይወት ተስፋ እንደ አምልኮት ያለውን እውነት እንዲያውቁ የተላከ፤ ስለዚህም ሕይወት የማይዋሽ እግዚአብሔር ከዘላለም ዘመናት በፊት ተስፋ ሰጠ፥

3. በዘመኑም ጊዜ፥ መድኃኒታችን እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ ለእኔ አደራ በተሰጠኝ ስብከት ቃሉን ገለጠ፤

4. በሃይማኖት ኅብረት እውነተኛ ልጄ ለሚሆን ለቲቶ፤ ከእግዚአብሔር አብ ከመድኃኒታችንም ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ምሕረት ሰላምም ይሁን።

5. ስለዚህ ምክንያት የቀረውን እንድታደራጅ በየከተማውም፥ እኔ አንተን እንዳዘዝሁ፥ ሽማግሌዎችን እንድትሾም በቀርጤስ ተውሁህ፤

6. የማይነቀፍና የአንዲት ሚስት ባል የሚሆን፥ የሚያምኑም ልጆች ያሉት፥ ስለ መዳራትም ወይም ስለ አለመታዘዝ የማይከሰስ ማንም ቢኖር፥ ሹመው።

7. ኤጲስ ቆጶስ፥ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ፥ የማይነቀፍ ሊሆን ይገባዋልና፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ፥ ነውረኛ ረብ የማይወድ፥

8. ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚገዛ ይሁን፤

9. ሕይወት በሚገኝበት ትምህርት ደግሞ ሊመክር ተቃዋሚዎቹንም ሊወቅስ ይችል ዘንድ፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና።

10. የማይታዘዙና ከንቱ የሚናገሩ የሚያታልሉ ይልቁንም ከተገረዙት ወገን የሚሆኑ ብዙ ናቸውና፤

11. እነዚህም ስለ ነውረኛ ረብ የማይገባውን እያስተማሩ ቤቶችን በሞላው ስለ ሚገለብጡ፥ አፋቸውን መዝጋት ይገባል።

12. የገዛ ራሳቸው ነቢይ የሆነ ከእነርሱ አንዱ። የቀርጤስ ሰዎች ዘወትር ውሸተኞች፥ ክፉዎች አራዊት፥ በላተኞች፥ ሥራ ፈቶች ናቸው ብሎአል።

13.

14. ይህ ምስክር እውነተኛ ነው። ስለዚህ ምክንያት የአይሁድን ተረትና ከእውነት ፈቀቅ የሚሉትን ሰዎች ትእዛዝ ሳያዳምጡ፥ በሃይማኖት ጤናሞች እንዲሆኑ በብርቱ ውቀሳቸው።

15. ሁሉ ለንጹሖች ንጹሕ ነው፤ ለርኵሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም የለም፥ ነገር ግን አእምሮአቸውም ሕሊናቸውም ረክሶአል።

16. እግዚአብሔርን እንዲያውቁ በግልጥ ይናገራሉ፥ ዳሩ ግን የሚያስጸይፉና የማይታዘዙ ለበጎ ሥራም ሁሉ የማይበቁ ስለ ሆኑ፥ በሥራቸው ይክዱታል።

About ቲቶ Chapter 1

Read ቲቶ Chapter 1 online from the Holy Bible. This chapter is part of the Book of ቲቶ in the New Testament. Continue reading with the chapter navigation above or explore the complete book.

Book Information

Book: ቲቶ
Chapter: 1
Testament: New Testament

How to Read this Chapter

Use the Previous and Next Chapter buttons to continue reading ቲቶ. You can also adjust the font size for comfortable reading and browse other books of the Bible using the navigation links.

https://www.youtube.com/watch?v=rzsT_Q3KLzE

More Resources

Continue Reading the Bible

Continue reading ቲቶ Chapter 1 and explore every book, chapter and verse of the Holy Bible. Use the navigation links above and below to move through the Scriptures with ease.

Frequently Asked Questions

What is ቲቶ Chapter 1?

ቲቶ Chapter 1 is part of the Book of ቲቶ in the Holy Bible.

Can I read this chapter online?

Yes. You can read the complete ቲቶ Chapter 1 online for free with easy chapter navigation.

More Chapters from ቲቶ

  1. ቲቶ Chapter 2
  2. ቲቶ Chapter 3

Explore More from አዲስ ኪዳን

  1. ዮሐንስ Chapter 9
  2. 1 ጴጥሮስ Chapter 3
  3. 1 ተሰሎንቄ Chapter 4
  4. የሐዋርያት ሥራ Chapter 7
  5. 1 ዮሐንስ Chapter 5
  6. ራእይ Chapter 17
  7. ኤፌሶን Chapter 1

Related Chapters & Readings

  1. ዘጸአት Chapter 16
  2. መዝሙረ ዳዊት Chapter 46
  3. ኢሳይያስ Chapter 7
  4. 1 ሳሙኤል Chapter 2
  5. ገላትያ Chapter 3
  6. ምሳሌ Chapter 21
  7. መሳፍንት Chapter 4
Share Your Love

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *